ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
Available in 53 languages
«ከሱለይማን ቢን ሱረድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጋር ተቀምጬ ሳለ ሁለት ሰዎች ይሰዳደባሉ። አንዱ ፊቱ ቀልቷል፣ ደም ስሩ ተገታትሯል። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ "እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።" ለርሱም ሄደው "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና "ከሸይጧን በአላህ ተጠበቅ" እያሉህ ነው።" አሉት። እርሱም "እኔ ላይ እብደት አለብኝ እንዴ?" አላቸው።»»Meaning translation ·
Saved at original quality







