Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 54 languages
«ከአቡ ቀታዳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በእንቅልፍ የሚያስደስት መልካም ህልም መመልከት ከአላህ እንደሆነና የሚጠላውንና የሚያሳዝነውን ቅብዥር መመልከት ደግሞ ከሸይጧን እንደሆነ ተናገሩ። የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ሰው ወደ ግራው አቅጣጫ ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ቅብዥሩን ተከትሎ ከሚመጡ ጎጂዎች ሰላም ለመሆን የተጠቀሰውን ማድረግ አላህ ሰበብ ስላደረገው እርሷ አትጎዳውም።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality