ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
Available in 61 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "አንድ የገጠር ሰው ወደ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመምጣት እንዲህ አለ: ' ብሰራው ጀነት የምገባበትን ስራ ጠቁሙኝ!' እርሳቸውም እንዲህ አሉት 'በርሱ ላይ አንዳችም ሳታጋራበት አሏህን ማምለክ፣ ግዴታ ሶላትን መስገድ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን መጾም ነው።' እርሱም "ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! ከዚህ ምንም አልጨምርም።' ብሎ ዞሮ የሄደ ጊዜ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ 'ከጀነት ባለቤቶች የሆነን ሰው መመልከት ያስደሰተው ወደዚህ ሰውዬ ይመልከት።' አሉ።"»Meaning translation ·
Saved at original quality








