Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦

Available in 45 languages
«ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ "ፀጉረ ጨብራራና ከበር ተገፍትሮ የሚባረር በአላህ ሲምል ግን አላህ ከመሃላው የሚያጠራው ስንትና ስንት ሰው አለ?!"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከሰዎች መካከል ፀጉሩ አመዳም የሆነና የተቆጣጠረ፤ ቅባትም የማይቀባውና አብዝቶ የማይታጠበው፤ ሰዎች ዘንድ ቦታ ስለሌለው አሳንሰውም ስለሚያዩት ከበራቸው የሚገፈትሩትና የሚያባሩት አይነት ሰው እንዳለ ነገር ግን ይህ ሰው አንድ ነገር እንደሚከሰት ቢምል መሃላው እንዳይፈርስና በዛም ተጠያቂነት እንዳይመጣበት አላህ እርሱን በማክበር መሃላውን ከማፍረስ ሊታደገው ዘንድ ጉዳዩን ተቀብሎ የማለበት ነገር እንዲከሰት የሚያደርግለት ሰው ነው። ይህም አላህ ዘንድ ደረጃና ክብር ስላለው መሆኑን ብለው ተናገሩ።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality