Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡

Available in 71 languages
«አቢ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ላይ አምስት መብቶች አሉት፤ ሰላምታ መመለስ፣ ህመምተኛ መጠየቅ፣ ጀናዛን መሸኘት፣ ጥሪውን መቀበልና ባስነጠሰው ጊዜ 'የርሐሙከሏህ' ማለት ናቸው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም በሌላኛው ሙስሊም ወንድሙ ላይ ያለውን ጥቂት መብቶች ገለፁ። ከነዚህ መብቶች መካከል የመጀመሪያው ሰላምታ ለሰጠህ ሰላምታን መመለስ ነው። ሁለተኛው መብት፡ ህመምተኛን መጠየቅና መዘየር ነው። ሶስተኛው መብት፡ ጀናዛን ከቤቱ ወደ ሚሰገድበት ከዚያም ወደ መቃብሩ ተወስዶ እስኪቀበር ድረስ መሸኘት ነው። አራተኛው መብት፡ ለሰርግም ይሁን ለሌላ ግብዣ ሲጠራ ጥሪውን አክብሮ ምላሽ መስጠት ነው። አምስተኛ መብት፡ ሲያስነጥስ "ተሽሚት" ሊያደርግ ሲሆን ይኸውም አስነጥሶ "አልሐምዱሊላህ" (ትርጉሙም፡ ምስጋና ለአላህ ይገባው) ካለ "የርሐሙከሏህ" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይዘንልህ) ይበለው፤ ከዚያም ያስነጠሰውም መልሶ "የህዲኩሙሏሁ ወዩስሊሕ ባለኩም" (ትርጉሙም፡ አሏህ ይምራህ ጉዳይህንም ያስተካክልልህ) ይላል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality