Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:

Available in 43 languages
«ከኢብኑ ዑመር ረዺየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አላህ የትንሳኤ ቀን የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ የሁሉም ከዳተኛ አርማው (ባንዲራው) ከፍ ይደረጋል። "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የፈፀመው ከዳተኝነቱ ነው።" ይባላልም።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላህ የትንሳኤ ቀን ለሒሳብ ብሎ የመጀመሪያዎቹንም የመጨረሻዎቹንም የሰበሰበ ጊዜ ከአላህ ጋር ወይም ከሰዎች ጋር ሊሞላው ቃል የገባውን ቃል ኪዳን ላልሞላ ከዳተኛ ሁሉ ከዳተኝነቱ የሚጋለጥበት አርማ ይተከላል። በዛን እለትም በአርማው ላይ እንዲህ ተብሎ ይለፈፋል: "ይህ እከሌ የእከሌ ልጅ የከዳው ክዳት ነው።" ይህም የትንሳኤ ቀን ለተሰበሰቡ ሰዎች መጥፎ ስራውን ለማሳየት ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality