Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:

Available in 60 languages
«ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ሰሐቦች (አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና) በአላህ መንገድ መታገልንና ጠላቶችን መጋደልን እጅግ በላጭ ከሆኑ ተግባራቶች መካከል እንደሆነ አድርገው ይመለከቱ ነበር። ዓኢሻም (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶችም ጂሃድ ማድረግ ሊፈቀድላቸው ዘንድ ጠየቀች። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሴቶች እጅግ በላጭ የሆነውን ጂሀድ ጠቆሟቸው: እርሱም ቁርኣንና ሐዲሥን የገጠመውና ከወንጀልና ከይዩልኝ የፀዳው ተቀባይነት ያለውን ሐጅ ነው።

Source
ቡኻሪ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality