Hadith for the World
ሐጅና ዑምራ

የሐጅና ዑምራ ትሩፋት

5 hadiths

5 hadiths

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው፡ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ብሏል፦ "ግንኙነትና ፆታዊ ስሜትን የሚያነሳሱን ሳይፈፅምና ሳያምፅ ለአሏህ ሐጅ አድርጎ የተመለሰ ልክ እናቱ እንደወለደችው ቀን (ከወንጀል ንፁህ) ሆኖ ይመለሳል።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከምእመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ጂሀድን እጅግ በላጭ ስራ አድርገን ነው የምናስበውና እኛም (ሴቶች) ከሀዲያንን እንታገልን?" እርሳቸውም፦ "በፍፁም! ነገር ግን እጅግ በላጩን ጂሀድ (ታገሉ!) (እርሱም) ተቀባይነት ያለው ሐጅ ነው።" አሉ።ቡኻሪ ዘግበውታል።
عن عائشة رضي الله عنها مرفوعاً: «ما مِن يومٍ أكثر مِن أنْ يُعْتِقَ اللهُ فيه عبدًا مِن النارِ، مِن يومِ عرفة، وإنَّه ليدنو، ثم يُباهي بهم الملائكةَ، فيقول: ما أراد هؤلاء؟».رواه مسلم
عن أبي هريرة رضي الله عنه: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: «العمرة إلى العمرة كفارةٌ لما بينهما، والحج المبرور ليس له جزاءٌ إلا الجنة».متفق عليه