Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 60 languages
«ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢብኑ ዐባስ በስሟ ጠርቶ ለነገረኝ እኔ ግን ስሟን ለራሳኋት አንዲት የአንሷር ሴት እንዲህ አሏት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" እርሷም "እኛ ከሁለት ግመል በቀር ሌላ አልነበረንም። የልጇ አባትና ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ አደረጉበት፤ ውሃ የምናመላልስበትን አንድ ግመል ደግሞ ለኛ ተወልን።" አለች። እርሳቸውም "ረመዳን የመጣ ጊዜ ዑምራ አድርጊ። በረመዳን የሚደረግ ዑምራ ሐጅ ከማድረግ ጋር ይስተካከላል።" አሏት።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከመሰናበቻ ሐጅ የተመለሱ ጊዜ ሐጅ ላላደረገች ከአንሷር ለሆነች ሴት "ከኛ ጋር ሐጅ ከማድረግ የከለከለሽ ምንድን ነው?" አሏት። ሁለት ግመል እንደነበራቸው፤ ባሏና ወንድ ልጇ በአንዱ ግመል ላይ ሐጅ እንዳደረጉና ሌላኛውን ደግሞ ከጉድጓድ ውሃ እንዲያመላልሱበት እንደተወላቸው በመንገር ያልሄደችበትን ምክንያቷን ገለፀችላቸው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዑምራን በረመዳን ወር በመፈፀም የሚገኘው ምንዳ የሐጅን ምንዳ የሚስተካከል እንደሆነ ነገሯት።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality