Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 60 languages
«ከጃቢር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። ስስታምነት ደማቸውን እንዲያፈሱና ሐራም (ያልተፈቀደውን) እንደ ሐላል አድርገው እንዲቆጥሩ አነሳስቷቸዋልና።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከበደል አስጠነቀቁ። ከበደል መካከልም: ሰዎችን መበደል፣ ነፍስን መበደል፣ በአላህ ሐቅ ላይ በደል መፈፀም ይጠቀሳሉ። በደል ማለት ሁሉንም የሐቅ ባለቤቶችን ሐቃቸውን ከመስጠት መተው ነው። በደል የትንሳኤ ቀን በባለቤቱ ላይ ከሚያጋጥመው መከራዎችና አስፈሪ ክስተቶች አኳያ ጨለማ ነው። ከስስትም ከለከሉ። እርሱም ከመጓጓት (መንሰፍሰፍ) ጋር እጅግ ስስታምነት ነው። ከስስታምነት መካከል: ገንዘባዊ ሐቆችን ከመወጣት ቸል ማለትና ለዱንያ እጅግ መንገብገብም ይጠቀሳል። ይህኛው የበደል ክፍል ማለትም ስስታምነት ከእኛ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷቸዋል። ይህም ከፊሉ ከፊሉን እንዲገድሉና አላህ እርም ያደረጋቸውን ክልክሎች የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳስቷቸዋል።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality