Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦

Available in 66 languages
«ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ "ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለጌ (ጸያፍ) አልነበሩም፣ ጸያፍ ቃላትም አይናገሩም። እንዲህም ይሉ ነበር: ' ከናንተ ምርጡ ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ከነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነምግባር መካከል ፀያፍ መናገር ወይም ፀያፍ ድርጊት አይገኝም ነበር። ትዝም አይላቸው። እሳቸው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የላቀ ስነምግባር ባለቤት ነበሩ። ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይሉ ነበር: "አላህ ዘንድ ከናንተ መካከል በላጩ መልካምን በመለገስ፣ ፊቱን በመፍታት፣ ሰውን ከማወክ በመቆጠብና የነሱን ክፋት በመቻል እንዲሁም ሰዎች ጋር ባማረ መልኩ በመኗኗር ስነምግባሩ እጅግ ያማረው ነው።"

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality