Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:-

Available in 60 languages
«ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:- "አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው በላጩ? ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም ሁለት ነገሮችን ጠቀሱ። የመጀመሪያው: ድሃዎችን ማብላትን ማብዛት ነው። እዚህ ውስጥም ሶደቃ፣ ስጦታ፣ ግብዣ፣ የሰርግ ድግስ ይገባሉ። የማብላቱ በላጭነትም በረሃብና ኑሮ በተወደደበት ወቅት የጠነከረ ይሆናል። ሁለተኛው: አወቅከውም አላወቅከውም በሁሉም ሙስሊም ላይ ሰላምታን ማቅረብ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality