Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 60 languages
«ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት! ወንድ ልጅ ከሌላ ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አይጠቅለል! ሴት ልጅም ከሌላ ሴት ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ አትጠቅለል!"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ( የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ወደ ሌላ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቱን ወይም ሴት ልጅ ወደ ሌላ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ መመልከቷን ከለከሉ። ሀፍረተ ገላ ማለት: ግልፅ የሆነ ጊዜ የሚያሳፍር የሆነ አካል ሁሉ ነው። የወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ ከእምብርት እስከ ጉልበቱ ሲሆን፤ የሴት ልጅ ደግሞ ከባዕድ ወንዶች አንፃር ሁሉም ሰውነቷ ሀፍረተ ገላ ነው። ከሴቶችና ከዘመዶቿ አንፃር ደግሞ በተለምዶ ቤት ውስጥ ስሰራ ግልፅ የሚሆነውን ያክል ግልፅ ታደርጋለች። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ወንድ ልጅ ተራቁቶ ከሌላው ወንድ ጋር በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ሴት ልጅም ተራቁታ ወደ ሴት ልጅ በአንድ ልብስ ውስጥ ወይም ለብቻቸው ከአንድ ብርድ ልብስ ስር መገለላቸውን ከለከሉ። ምክንያቱም ይህ አንዱ የሌላኛው ጓደኛውን ሀፍረተ ገላ ወደመንካት ያደርሰዋልና። መንካቱ ደግሞ እንደማየቱ ክልክል ነው። እንደውም ወደ ትልቅ ብክለት ስለሚያመራ መንካቱ ከማየትም በበለጠ ክልክል ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality