Hadith for the World
Tap the image to view it full size
የተከበረው ቁርአንና ከቁርአን ጋር የተያያዙ እውቀቶች

ከዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና -እንደተላለፈው፡ "የአሏህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፡

Available in 42 languages
«ከዓኢሻህ ረዲየሏሁ ዐንሃ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና -እንደተላለፈው፡ "የአሏህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፡ "ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብ ሰው የተከበሩና ታዛዥ ከሆኑ መላዕክቶች ጋር ነው፤ ቁርኣንን ሲያነብ ከብዶት እየተቸገረ የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ አለው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቁርአንን ሽምደዳውን አሳምሮ፤ አስተማማኝ በሆነ መልኩ፤ ውብና ቆንጆ አድርጎ የሚያነብ ሰው በመጪው ዓለም ያለው ምንዳ ደረጃው ታዛዥና የተከበሩ ከሆኑ መላእክቶች ጋር እንደሆነ፤ ቁርአንን የመሸምደድ አቅሙ ደካማ ስለሆነ ቁርአን ማንበብ በርሱ ላይ ከባድና አስቸጋሪ ሆኖበት እየተንተባተበና እየመላለሰ የሚያነብ ከመሆኑም ጋር ሳያቋርጥ ዘውትር የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ እንዳለው ተናገሩ። አንዱ ምንዳ የማንበቡ ምንዳ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ የመላለሰበትና ተቸግሮ የማንበቡ ምንዳ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality