የተከበረው ቁርአንና ከቁርአን ጋር የተያያዙ እውቀቶች
ከአቡ ኡማመተል ባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
Available in 38 languages
«ከአቡ ኡማመተል ባሂሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "ቁርአንን ቅሩ! እርሱ የትንሳኤ ቀን ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል። ሁለቱን አብሪ የሆኑ ምዕራፎች ሱረቱል በቀራንና አሉ ዒምራንን ቅሩ። እነርሱ የትንሳኤ ቀን ልክ ደመና ወይም ጥላ መስለው ወይም ተጠባብቀው ረድፍ የሰሩ የወፎች ሁለት መንጋ መስለው ይመጣሉ። ለባለቤቶቻቸውም ይሟገታሉ። የበቀራን ምዕራፍ ቅሩ! እርሷን መያዝ በረከት ነው። እርሷን መተው ደግሞ የሚያስቆጭ ነው። ደጋሚዎችም አይችሏትም።"»»Meaning translation ·
Saved at original quality








