Hadith for the World
Tap the image to view it full size
የተከበረው ቁርአንና ከቁርአን ጋር የተያያዙ እውቀቶች

ከኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

Available in 70 languages
«ከኡበይ ቢን ከዕብ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ውስጥ ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አልኳቸው። " እርሳቸውም በድጋሚ "አቡ ሙንዚር ሆይ! ከአላህ መጽሐፍ ከሸመደድከው ማንኛው አንቀፅ ታላቅ እንደሆነ ታውቃለህን?" አሉኝ። "{አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} [አልበቀራህ: 255]" (አያተል ኩርሲይ) አልኩኝ። እሳቸውም ደረቴን በመምታት "በአላህ እምላለሁ! እውቀት ያስደስትህ አቡ ሙንዚር!" አሉኝ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ኡበይ ቢን ከዕብን የአላህ መጽሐፍ ውስጥ ትልቁ አንቀፅ ማን ናት? በማለት ጠየቁት። መልስ ለመስጠት ካመነታ በኋላ አየቱል ኩርሲይ ናት {አላህ ከእርሱ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው።} በማለት መለሰ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በዕውቀትና ጥበብ የተሞላ መሆኑን ለመጠቆም ደረቱን በመምታት በዚህ ዕውቀት እንዲደሰትና እንዲገራለት ዱዐ በማድረግ ትክክለኛ መልስ እንደመለሰ በመጥቀስ አበረታቱት።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality