Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:

Available in 48 languages
«ከአቡ ሙሳ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ስለአንዳንድ የጀነት ፀጋዎች ተናገሩ። ጀነት ውስጥ ለአማኞች ትልቅና ውስጡ ሰፊ የሆነ ከአንድ ውስጡ ባዶ ከሆነ ወጥ ሉል ድንኳን ተዘጋጅቶላቸዋል። ወደ ሰማይ አግድመቱና ርዝመቱ ስልሳ ማይል የሚሆን ነው። ከአራት ማዕዘን ጎኖቹ መካከል በየሁሉም ጎንና ጥግ ሚስቶች አሉት። አንዳቸው ከአንዳቸው ጋር አይተያዩም። አማኙም በመካከላቸው ለግንኙነት ይዞራል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality