Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦

Available in 63 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦ "በመናፍቃን ላይ እጅግ ከባዱ ሶላት የዒሻእ ሶላትና የፈጅር ሶላት ናቸው። በውስጧ ያለውን ምንዳ ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን ይመጡ ነበር። በርግጥ ሶላት እንዲሰገድ አዝዤ፤ ሰዎችን እንዲያሰግድም አንድ ሰው ላዝ፤ ከዚያም ሶላትን በመስጂድ ተገኝተው ወደማይሰግዱ ሰዎች ቤት የታሰረ እንጨት ከያዙ ወንዶች ጋር በመሄድ በነሱ ላይ ቤቶቻቸውን በእሳት ላቃጥል አስቤም ነበር።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለሙናፊቆችና ሶላትን በጀማዓ መገኘት ላይ በተለይ የዒሻእና ፈጅር ሶላት ላይ ስላላቸው ስንፍና፤ እነርሱ ሁለቱን ሶላት ከሙስሊም ጀመዓ ጋር መስገድ የሚያስገኘውን አጅር እና ምንዳ መጠን ቢያውቁ ኖሮ ህፃን ልጅ በሁለት እጆቹና ጉልበቱ እንደሚዳኸው እንሱም እየዳኹ ይመጡ እንደነበር ተናገሩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ኢቃም እንድትባል አዘው በሳቸው ምትክ አንድ የሚያሰግድ ሰው ሊመድቡና ከዚያም የታሰረ እንጨት ከተሸከሙ ሰዎች ጋር በመሆን ጀመዓ ሶላት ወደማይገኙ ወንዶች ሂደው ጀመዓ ባለመገኘት የሰሩት ወንጀል ከባድ ስለሆነ ቤታቸውን በእሳት ሊያቃጥሉ ቆርጠው ነበር። ነገር ግን ቤት ውስጥ ንፁህ ሴቶች፣ ህፃናትና ሌሎችም የሚያስቀር ምክንያት ያላቸው ስላሉ አላደረጉትም።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality