Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተለለፈው እንዲህ ብለዋል:

Available in 71 languages
«ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተለለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን በምልጃቸው ከሰዎች ሁሉ የበለጠ እድለኛ የሚሆኑት "ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት" ማለትም ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው እንደሌለ አምነው ከሽርክ ይሁን ከይዩልኝና ይስሙልኝም ጥርት ያሉት መሆናቸውን ተናገሩ።

Source
ቡኻሪ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality