Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከጃቢር ቢን ዓብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 55 languages
«ከጃቢር ቢን ዓብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከኔ በፊት አንድም አካል ያልተሰጠው አምስት ነገሮችን ለኔ ተሰጥተውኛል። የወር መንገድ ሲቀር (ጠላቶች ውስጥ) ፍርሃት በመክተት ተረድቻለሁ፤ ምድር ለኔ መስገጃም ንፅህና መጠበቂያም ተደርጋልኛለች። ስለዚህ ከኡመቴ ማንኛውም ሰው ሶላት ከደረሰችበት ይስገድ። ምርኮ ለኔ ተፈቅዷል፤ ከኔ በፊት ለአንድም አካል አልተፈቀደችም። ምልጃ ተሰጥቶኛል። ነቢይ የሚላከው ወደ ህዝቦቹ ብቻ ነበር። እኔ ግን ወደ ሰው ባጠቃላይ ተልኬያለሁ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከርሳቸው በፊት ለነበረ ለአንድም ነቢይ ያልተሰጡ አምስት ነገሮች አላህ ለርሳቸው እንደሰጠ ተናገሩ: የመጀመሪያው: በፍርሃት ተረድቼያለሁ። በኔና በነርሱ መካከል የወር መንገድ ቢቀር ራሱ የጠላቶቼን ልብ ፍርሃት ይወራቸዋል። ሁለተኛው: ምድር ለኛ መስጂድ ተደርጋለች። የትም ብንሆን እንሰግዳለን። ውሃ መጠቀም በተሳነን ጊዜ ደሞ አፈሯ መፅጃ ተደርጎልናል። ሶስተኛ: ለኛ የጦርነት ምርኮ ተፈቅዶልናል። ይህም ሙስሊሞች ከከሃዲዎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት የሚማርኩት ንብረት ነው። አራተኛ: ሰዎችን ከትንሳኤ ቀን መቆም ጭንቀት የምገላግልበት ትልቁ ምልጃ ተሰጥቶኛል። አምስተኛ: ወደ ፍጡራን ባጠቃላይ ወደ ሰዉም ወደ ጂኑም ሁሉ ተልኬያለሁ። ይህም ከርሳቸው በፊት ከነበሩት ነቢያት ተቃራኒ መሆኑ ነው። እነርሱ ይላኩ የነበሩት ወደ ህዝባቸው ብቻ ነበርና።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality