AM
በአላህ ማመን
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል
14 hadiths
አላህን በጌትነቱ መነጠል
2
አላህን በተመላኪነቱ መነጠል
14
አላህን በስሞቹና በባህሪያቱ መነጠል
24
14 hadiths
ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።' ዑመርም 'በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲከለክሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ራሴ በመናገርም ይሁን የሌላ ሰውን መሀላ ሳስተላልፍ በከለከሉት ምዬ አላውቅም።' አሉ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፡ ' እኔ በሽርክና ከመጋራት ከተብቃቁ ሁሉ እጅግ የተብቃቃሁ ነኝ። ከኔ ጋር ሌላን አጋርቶ ስራን የሰራ እሱንም ማጋራቱንም እተወዋለሁ።'"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡ "ክርስቲያኖች የመርየም ልጅን ሲያሞግሱ ወሰን እንዳለፉት እኔን ስታሞግሱ ወሰን አትለፉ። እኔ የአሏህ ባሪያ ብቻ ነኝ። ስለዚህም የአላህ ባሪያና መልክተኛው በሉኝ።'"
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተለለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የቂያማ ቀን በርሶ ምልጃ ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛው ማን ነው?" ተባሉ። የአላህ መልክተኛም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ፡- 'አቡ ሁረይራ ሆይ! ባንተ ላይ ካየሁት የሐዲሥ ጉጉት አንፃር ይህንን ጥያቄ ለመጠየቅ የሚቀድምህ አይኖርም ብዬ አስቤ ነበር። የቂያማ ቀን በኔ አማላጅነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ እድለኛ የሚሆኑት ጥርት ባለ መልኩ ከልባቸው ወይም ከነፍሳቸው 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ያሉት ናቸው።'"
ቡኻሪ ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንዷን ተናገሩ እኔ ደግሞ ሌላዋን ተናገርኩ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: ‹ ከአላህ ውጪ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) እየተጣራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።› እኔ ደግሞ: ‹ለአላህ ሌላን ቢጤን (ባላንጣን) ሳይጣራ የሞተ ሰው ጀነት ይገባል።› አልኩኝ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن ابن مسعود رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : «من أصابته فَاقَة فأنْزَلها بالناس لم تُسَدَّ فَاقَتُهُ، ومن أنْزَلها بالله، فَيُوشِكُ الله له بِرزق عاجل أو آجل».
رواه أبو داود والترمذي وأحمد
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم أنه قال: "أكبر الكبائر: الإشراك بالله، والأمن من مَكْرِ الله، والقُنُوطُ من رحمة الله، واليَأْسُ من رَوْحِ الله".
رواه عبد الرزاق
عن عبد الله بن عكيم رضي الله عنه مرفوعاً: «مَنْ تَعَلَّقَ شيئا وُكِلَ إليه».
رواه أحمد والترمذي
ከጧሪቅ ቢን አሽየም አልአሽጀዒይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህን መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: 'ላኢላሃ ኢለሏህ ብሎ ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ነገሮች የካደ ሰው ገንዘቡም ደሙም እርም ይሆናል። ሂሳቡ ያለው አላህ ላይ ነው።'"
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ መርሠድ አልጘነዊይ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'መቃብሮች ላይ አትቀመጡ! ወደርሷም አትስገዱ!'"
ሙስሊም ዘግበውታል።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ሙዓዝ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ : ከነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ኋላ ዑፈይር የሚባለው አህያ ላይ ተፈናጥጬ ሳለው "ሙዓዝ ሆይ አላህ በባሮቹ ላይ ያለውን ሐቅ፤ ባሮችስ አላህ ዘንድ ያላቸውን ሐቅ ታውቃለህን? " አሉ። "አላህና መልክተኛው ይወቁ !" አልኩኝ። እሳቸውም "አላህ በባሮቹ ላይ ያለው ሐቅ ሊገዙትና በሱ ላይም አንዳችንም ላያጋሩ ሲሆን፤ ባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ ደግሞ በሱ ላይ አንዳችንም ያላጋራን ላይቀጣ ነው።" አሉ። "የአላህ መልክተኛ ሆይ ሰዎችን ላበስራቸውን?" አልኳቸው። እሳቸውም "አታበስራቸው (በዚህ ስራ ላይ ብቻ) ይደገፋሉ (ይሳነፋሉ)። " አሉ።
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ አንድ ሰውዬ በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለቱ (ጀነትና እሳት ውስጥ መግባትን) የሚያስወስኑ ነገሮች ምንድናቸው?" እሳቸውም "በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።
ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ለናንተ ሶስት ነገር ይወድላችኋል፤ ሶስት ነገርንም ይጠላባችኋል። እርሱን መገዛታችሁን፣ በርሱ ላይ አንዳችንም አለማጋራታችሁን፣ ሁላችሁም በአላህ ገመድ መተሳሰራችሁንና አለመለያየታችሁን ለናንተ ይወድላችኋል። አሉባልታን፣ ጥያቄ ማብዛትንና ገንዘብ ማባከንን በናንተ ላይ ይጠላባችኋል።"»
ሙስሊም ዘግበውታል።