Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦

Available in 71 languages
«ጃቢር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ አንድ ሰውዬ በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ሁለቱ (ጀነትና እሳት ውስጥ መግባትን) የሚያስወስኑ ነገሮች ምንድናቸው?" እሳቸውም "በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት ገባ፤ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት ገባ።" አሉ።»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

አንድ ሰውዬ ነቢዩን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጀነት መግባትን ስለሚያስወስን እና እሳት መግባትን ስለሚያወስን ሁለት ነገሮች ጠየቃቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና፦ ጀነትን የሚያስወስነው ነገር ሰውዬው አላህን በብቸኝነት እያመለከ በሱ አንዳችንም ሳያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት። እሳትን የሚያስወስነው ነገር ደግሞ ሰውዬው ለአላህ በተመላኪነቱ ወይም በጌትነቱ ወይም በስሞቹና ባህሪያቶቹ አምሳያ እና አቻ በማድረግ በአላህ ላይ አንዳችን ነገር እያጋራ መሞቱ ነው ብለው መለሱለት።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality