Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዐስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦

Available in 71 languages
«ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዐስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "አላህ ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት የፍጡራንን ውሳኔ ፅፏል።" እንዲህም አሉ፦ " ዐርሹ ውኃ ላይ ነው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በፍጡራኖች ላይ የሚከሰተውን ውሳኔዎች ህይወት፣ ሞት፣ ሲሳይና ሌሎችንም ሰማያትንና ምድርን ከመፍጠሩ ከሀምሳ ሺህ ዓመት በፊት በዝርዝር በጥብቅ ሰሌዳ ውስጥ እንደፃፈውና እሱም አላህ በወሰነው መልኩ የሚከሰት መሆኑን ተናገሩ። ሁሉም የሚከሰቱ ነገሮች በአላህ ፍርድና ውሳኔ መሰረት ነው። አንድ ሰውን ያገኘው ነገር ቀድሞውኑ ሊስተው አይችልም ነበር፤ የሳተውም ነገር ሊያገኘው አይችልም ነበር።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality