Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦

Available in 61 languages
«ከዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።' ዑመርም 'በአላህ እምላለሁ! የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሲከለክሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ እኔ ራሴ በመናገርም ይሁን የሌላ ሰውን መሀላ ሳስተላልፍ በከለከሉት ምዬ አላውቅም።' አሉ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ በአባት መማልን እንደሚከለክል ተናገሩ። ስለዚህም መማል የፈለገ ሰው በአላህ ካልሆነ በቀር በሌላ አይማል። ቀጥለውም ዑመር ቢን ኸጧብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲከለክሉ ከሰሙ ጀምሮ ሆን ብለውም ይሁን ሌላ ሰው ከአላህ ውጪ መማሉን በመናገር መልኩም ይሁን ምለው እንደማያውቁ አወሱ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality