Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:

Available in 59 languages
«ከመዕዳን ቢን አቢ ጦልሐ አልየዕመሪይ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ ነፃ ያወጡት ባሪያ የነበረውን ሠውባንን አገኘሁትና እንዲህ አልኩት: አላህ በርሱ ምክንያት ጀነት እንድገባ የሚያደርገኝን የምሰራውን ስራ ንገረኝ? ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆነውን ስራ ንገረኝ? እርሱም ዝም አለ። በድጋሚ ጠየቅኩት አሁንም ዝም አለ። አሁንም ለሶስተኛ ጊዜ ጠየቅኩት እርሱም: "ስለዚህ ጉዳይ የአላህን መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›"» መዕዳን እንዲህ አለ «ቀጥሎ አቡ ደርዳእን አገኘሁና ጠየቅኩት። እርሱም ሠውባን ያለኝን አምሳያ ነገረኝ።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጀነት ለመግባት ሰበብ ስለሆነ ወይም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስለሆነ ስራ ተጠየቁ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለጠያቂው እንዲህ አሉት: ሶላት ውስጥ ሱጁድ ማብዛትን አዘውትር! አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም ቢምርህ እንጂ አንድም ሱጁድ ለአላህ አትወርድም።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality