AM
ሶላት
የመስጊዶች ህግጋት
9 hadiths
የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ
5
የሶላት ትሩፋት
10
አዛንና ኢቃማህ
6
أوقات النهي عن الصلاة
2
የሶላት መስፈርቶች
3
የሰላት ማዕዘናት
2
Obligatory Acts of Prayer
1
سنن الصلاة
1
የሶላት አሰጋገድ
10
የሶላት አዝካሮች
15
مبطلات الصلاة
1
የሰጋጆች ስህተት
5
የመርሳት፣ የቲላዋህና የምስጋና ሱጁድ
4
የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት
7
የኢማምና የተከታይ ህግጋት
4
ባለ ዑዝር (ተቀባይነት ያለው ምክንያት ያላቸው ሰዎች) የሚሰግዱት አሰጋገድ
1
የጁሙዓ ሶላት
7
የፈቃደኝነት ሶላቶች
40
صلاة الكسوف والخسوف
2
صلاة الاستسقاء
1
የመስጊዶች ህግጋት
9
9 hadiths
ከአነስ ቢን ማሊክ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሰልፋችሁን አስተካክሉ! ሰልፍ ማስተካከል ሶላትን ከሚሞሉት መካከል ነውና።"»
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "አሏህ ሆይ! ቀብሬን ጣኦት አታድርግብኝ፤ የነቢያቶቻቸውን መቃብር መስገጃ አድርገው በያዙ ህዝቦች ላይ የአሏህ እርግማን ሰፈነባቸው።"
አሕመድ ዘግበውታል።
عن أبي ذر رضي الله عنه قال: قال النبي صلى الله عليه وسلم :«عُرِضَتْ عَلَيَّ أعمالُ أُمتي، حَسَنُهَا وسَيِّئُهَا فَوَجَدتُ في مَحَاسِنِ أَعْمَالِهَا الأَذَى يُمَاطُ عَنِ الطَّرِيقِ، ووَجَدتُ في مَسَاوِئِ أَعْمَالِهَا النُّخَاعَةُ تَكُونُ في المَسْجِدِ لا تُدْفَنُ».
رواه مسلم
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስፍራ መስጂዶች ናቸው። አላህ ዘንድ እጅግ የሚጠላው ስፍራ ገበያዎች ናቸው።"
ሙስሊም ዘግበውታል።
የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦ ኡሙ ሰላማ ለአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሀበሻ ምድር ማሪያህ በምትባል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላየቻቸው ምስሎች ነገረቻቸው። የአላህ መልዕክተኛም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ከመካከላቸው መልካም (ጻድቅ) ባርያ ወይም መልካም ሰው ሲሞት በመቃብሩ ላይ መስገጃን የሚገነቡና በውስጡም (ምስሉን) ስእላ ስእል የሚቀርፁ ናቸው። እነዚህ ህዝቦች አላህ ዘንድ እጅግ ክፉ (መጥፎ) ፍጡራን ናቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ቀታዳ አስሰለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ ይስገድ።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከአቡ ሑመይድ ወይም አቡ ኡሰይድ እንደተዘገበው እንዲህ አለ: "የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹አንዳችሁ መስጂድ የገባ ጊዜ: 'አልላሁምመፍተሕ ሊ አብዋበ ረሕመቲከ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! ለኔ የእዝነትህን በሮች ክፈትልኝ) ይበል። የወጣ ጊዜም ‘አልላሁምመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ' (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! እኔ ከትሩፋትህ እጠይቅሀለሁ።) ይበል።›"
ሙስሊም ዘግበውታል።
عَن أَبي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَامَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي صَلاَةٍ وَقُمْنَا مَعَهُ، فَقَالَ أَعْرَابِيٌّ وَهُوَ فِي الصَّلاَةِ: اللَّهُمَّ ارْحَمْنِي وَمُحَمَّدًا، وَلاَ تَرْحَمْ مَعَنَا أَحَدًا. فَلَمَّا سَلَّمَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ لِلْأَعْرَابِيِّ: «لَقَدْ حَجَّرْتَ وَاسِعًا» يُرِيدُ رَحْمَةَ اللهِ.
رواه البخاري
ከአቡ ሁረይራ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል: "ሰባት አካላቶች ከአላህ ጥላ በቀር ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ያስጠልላቸዋል። ፍትሃዊ መሪ፤ አላህን በማምለክ ያደገ ወጣት፤ ቀልቡ ወደ መስጂዶች የተንጠለጠለ ሰውዬ፤ በአላህ መንገድ የተገናኙ በርሱም መንገድ የተለያዩ ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሁለት ሰዎች፤ የተከበረችና ቆንጆ የሆነች ሴት ለዝሙት ጠርታው እኔ አላህን እፈራለሁ ያለ ሰውዬ፤ ቀኙ የምትሰጠውን ግራው እስከማታውቅ ድረስ ምፅዋቱን በመደበቅ ምፅዋት የመፀወተ ሰውዬ፤ አላህን ገለል ብሎ አውስቶ አይኖቹ ያነቡ ሰውዬ ናቸው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።