Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:

Available in 60 languages
«ከዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: 'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜ ልኩን ነው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

አንድም ሙስሊም የግዴታ ሶላት ወቅት የሚገባበትና ዉዱኡን አሳምሮና አሟልቶ የሚያደርግ፤ ቀጥሎም ቀልቡና አካሉ ሁሉ ወደ አላህ የዞሩና የአላህን ልቅና ያስተዋሉ በሚሆኑበት መልኩ በሶላቱ የሚመሰጥ፤ እንደ ሩኩዕ፣ ሱጁድና ሌሎችንም የመሳሰሉትን የሶላቱን ድርጊቶች የሚያሟላ አይሆንም ይህ ሶላቱ ላሳለፈው ትናንሽ ወንጀሎች ማስማሪያ ቢሆን እንጂ፤ ነገር ግን ይህ የሚሆነው ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል የሆነን አንድም ወንጀል እስካልሰራ ነው። ይህ ትሩፋትም ዘመናት በነጎዱ ቁጥር በሁሉም ሶላቶች ላይ እንደሚቀጥል ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገለፁ።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality