Hadith for the World
ስሞችና ህግጋት

የኢማን መጨመርና መቀነስ

5 hadiths

5 hadiths

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው። ሓያእ (አይነ አፋርነትም) የኢማን አንዱ ክፍል ነው።'"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።"ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- "ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"ሙስሊም ዘግበውታል።
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: "ثَلاَثٌ مَنْ كُنَّ فِيهِ وَجَدَ حَلاَوَةَ الإِيمَانِ: أَنْ يَكُونَ اللَّهُ وَرَسُولُهُ أَحَبَّ إِلَيْهِ مِمَّا سِوَاهُمَا، وَأَنْ يُحِبَّ المَرْءَ لاَ يُحِبُّهُ إِلَّا لِلَّهِ، وَأَنْ يَكْرَهَ أَنْ يَعُودَ فِي الكُفْرِ كَمَا يَكْرَهُ أَنْ يُقْذَفَ فِي النَّارِ".متفق عليه
ከዓባስ ቢን ዐብዱል ሙጦሊብ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰማቸው: "በአሏህ ጌትነት፣ በእስልምና ሃይማኖትነት እና በነቢዩ ሙሐመድ ነቢይነት የወደደ ሰው የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል።"ሙስሊም ዘግበውታል።