Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

Available in 65 languages
«ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ኢማን ሰባ ምናምን ወይም ስልሳ ምናምን ክፍሎች አሉት። በላጩ ክፍልም 'ላኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን ዝቅተኛው ክፍል መጥፎን ነገር ከመንገድ ላይ ማስወገድ ነው። ሓያእ (አይነ አፋርነትም) የኢማን አንዱ ክፍል ነው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ኢማን ተግባሮችን፣ እምነቶችንና ንግግሮችን የጠቀለለ ብዙ ክፍሎች እንዳሉት ተናገሩ። ከኢማን ክፍሎች ውስጥ በላጩና ከፍተኛው ትርጉሙን አውቆ ፣ የሚያስፈርደውን በመተግበር "ላኢላሃ ኢለሏህ" ማለት ነው። አላህ አንድና ብቸኛ አምላክ መሆኑንና ለአምልኮ የተገባ ብቸኛ አምላክ መሆኑን ከርሱ ውጪ ያለ ማንም አምልኮ እንደማይገባውም ማመን ነው። የኢማን ትንሹ ስራ ሰዎችን የሚያውክ የሆነን ነገር ሁሉ ከመንገዳቸው ላይ ማስወገድ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሓያእ (አይነ አፋርነት) የኢማን አንድ ክፍል መሆኑን ተናገሩ። ይህም መልካም ለመስራትና ፀያፍ ለመተው የሚያነሳሳ ባህሪ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality