Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡-

Available in 70 languages
«አቡ ሰዒድ አል'ኹድሪይ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ ፡- የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡- "ከእናንተ መካከል መጥፎ ሢሠራ የተመለከተ፥በእጁ ይለውጠው (ያስተካክለው)፤ ይህንን ካልቻለ በምላሱ ይከላከል፤ ይህንንም ካልቻለ በቀልቡ (ልቡ) ይጥላ ይህ ግን ደካማው የኢማን ክፍል ነው።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በቻልነው መጠን መጥፎ ነገርን እንድንለውጥ ( እንድናስወግድ) አዘዋል። መጥፎ ነገር የሚባለውም፥ አላህና መልክተኛው የከለከሏቸው ሁሉም ነገሮች ናቸው። መጥፎ ነገርን ከተመለከተ አቅም ካለው በእጁ የመለወጥ (የማስወግድ)ግዴታ አለበት። ይህን ማድረግ ከተሳነው ደግሞ መጥፎ ነገር ፈፃሚውን በመከልከል፣ ጉዳቱን ለሱ በማብራራት፣ ከዚህ እኩይ ተግባር ፈንታ እሱን ወደ መልካም በመምራት በአንደበቱ ይለውጠው። ይህኛዉ የመለወጥ እርከን ከተሳነውም ይህን መጥፎ ነገር በመጥላት፣ ለመለወጥ አቅም ቢኖረው ኖሮ እንደሚለውጠው በመቁረጥ በቀልቡ ይለውጠው። በቀልብ መለወጥ (መጥላት) መጥፎ ነገርን የመለወጥ እጅግ ደካማው የኢማን እርከን ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality