Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡ ኡማማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 59 languages
«ከአቡ ኡማማ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ አየቱል ኩርሲይን የቀራ ሰው ከሞት በቀር ጀነት ለመግባት ምንም እንደማይከለክለው ተናገሩ። ይህቺም አንቀጽ በበቀራ ምእራፍ ውስጥ የምትገኝ ሲሆን እርሷም ይህቺ የአላህ ቃል ናት: ትርጉሟ: {አላህ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም። ህያው ራሱን ቻይ ነው። ማንገላጀትም እንቅልፍም አትይዘውም። በሰማያት ውስጥና በምድር ውስጥ ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ ነው። ያ እርሱ ዘንድ በፍቃዱ ቢሆን እንጂ የሚያማልደው ማነው? (ከፍጡሮች) በፊታቸው ያለውንና ከኋላቸው ያለውን ሁሉ ያውቃል። በሻውም ነገር እንጂ ከእውቀቱ በምንም ነገር አያካብቡም። (አያውቁም)። መንበሩ ሰማያትንና ምድርን ሰፋ። ጥበቃቸውም አያቅተውም። እርሱም የሁሉ በላይ ታላቅ ነው።} [አልበቀራህ: 255]

Source
رواه النسائي في الكبرى
Download image

Saved at original quality