Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 59 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: «ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ግዴታ ሶላቶች ከተጠናቀቁ በኋላ እነዚህን ያለ ሰው የሚያገኘውን ምንዳ ገለፁ: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ሱብሓነላህ": ይህም አላህን ከጉድለቶች ሁሉ ማጥራት ነው። ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አልሐምዱ ሊላህ": ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቱ ማወደስ ነው። ሰላሳ ሶስት ጊዜ "አላሁ አክበር": ማለት ይህም አላህ ከሁሉም ነገር እጅግ የላቀ ነው ማለት ነው። መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ‐ ትርጉሙም፦ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የለውም። ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየና ከርሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ውዳሴና ሙገሳ ከውዴታና ልቅና ጋር የተገባው ነው። እርሱም ምንም የማይሳነው ቻይ ነው። እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ወንጀሉ ባህር በሚናወጥና በሚላተም ሰአት ከላይ በሚሆነው ነጭ አረፋ ልክ ቢበዛ ራሱ ትማራለችም ትሰረዛለችም።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality