Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 65 languages
«ከሠውባን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ ሶስት ጊዜ ኢስቲግፋር ያደርጉ (ምህረት ይጠይቁ) ነበር። እንዲህም ይሉ ነበር: 'አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም' ትርጉሙም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) ወሊድ ለአውዛዒይ 'እንዴት ነው ኢስቲግፋር የሚደረገው? አልኩት' አለ። እሳቸውም 'አሰተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ' በማለት ነው ብለው መለሱልኝ።' አለ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሶላታቸውን ያጠናቀቁ ጊዜ "አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ አስተግፊሩላህ" ይሉ ነበር። ቀጥለውም ጌታቸውን "አላሁመ አንተ አስሰላም ወሚንከ አስሰላም ተባረክተ ዘል ጀላሊ ወልኢክራም" (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ ሰላም የሚገኘውም ካንተ ነው። የግርማና ክብር ባለቤት የሆንከው ጠራህ!) በማለት ጌታቸውን ያልቃሉ። አላህ በባህሪያቶቹ የተሟላና ሰላም ነው፤ ከሁሉም ጉድለትና ነውርም የጠራ ነው። ከዱንያና አኺራ ክፋት ሰላም የሚፈለገውም ከሌላ ሳይሆን ከርሱ ነው። እርሱ ጥራት ይገባውና በሁለቱም ዓለም መልካሙ የበዛ ፣ የልቅናና መልካም ባለቤት ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality