Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

Available in 54 languages
«ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ አንድ ሶሐባ አንድ እፍኝ እህል ‐እፍኝ የተባለው መካከለኛ ሰው በሁለት እጆቹ የሚዘግነው መጠን ነው።‐ ወይም የእፍኙን ግማሽ እህል ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ ጋር እኩል እንደማይሆን ተናገሩ። ይህም ከፍተኛ ኢኽላስ ስላላቸው፣ መካ ከመከፈቱ በፊት መመፅወት እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዛ ወቅት በመመፅወታቸውና በመዋጋታቸው ስለቀደሙ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality