Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:

Available in 54 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው : ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: «ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ፀሐይ በምትወጣበት ቀናት ሁሉ ሁለት መልአኮች ወርደው እንደሚጣሩ ተናገሩ። አንደኛቸው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ! አላህን ለመታዘዝ፣ ለቤተሰቦቹ፣ ለእንግዶቹ፣ ለበጎ አድራጎት ለሚሰጥ ሰው ምትኩን ስጠው፤ ካወጠው የተሻለ ተካለትም ባርክለትም። ሌላኛው ደግሞ "አላህ ሆይ! ከመስጠት የሚቋጥርን ጥፋትን ስጠው፤ ለሚገባቸው ከመስጠት ገንዘቡን የነፈገንም ገንዘቡን አውድምበት!" ይላል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality