Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦

Available in 70 languages
«አቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "መወሰኛይቱን ሌሊት (ለይለቱል ቀድርን) በአላህ አምኖና ምንዳውን አስቦ የቆመ ሰው ያለፈው ኃጢዓቱ ይማርለታል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በረመዳን ከመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ውስጥ የምትገኘው መወሰኛይቱ ሌሊትን (ለይለቱል ቀድርን) የመቆም ትሩፋትን ተናገሩ። በዚህች ሌሊት በሷና ስለሷ ትሩፋት በመጡ ሐዲሦች አምኖ እንዲሁም በስራው ይዩልኝና ይስሙልኝን ሳይሆን የአላህን ምንዳ ከጅሎ በሶላት፣ በዱዓእ፣ ቁርአን በመቅራትና በዚክር የታገለ ሰው ያለፈውን ኃጢዓቱ ይማራል።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality