Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው:

Available in 51 languages
«የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ለይለተል ቀደርን በመፈለግ በመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናቶች ኢዕቲካፍ በማድረግ እንደሚያሳልፉ ይህንንም አላህ ሩሓቸውን እስከወሰደበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠሉበትና ከርሳቸው በኋላም ሚስቶቻቸው (ረዺየሏሁ ዐንሁነ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ኢዕቲካፍ ማድረጉን እንደቀጠሉበት ተናገረች።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality