Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 49 languages
«ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን በባሪያውም፣ በነፃውም፣ በወንዱም፣ በሴቱም፣ በህፃኑም፣ በትልቁም ሙስሊም ላይ ግዴታ አደረጉ። ሰዎች ወደ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከረመዷን በኋላ ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ። መጠኑም አራት እፍኝ የሚያህል አንድ ቁና ነው። አንድ እፍኝ፡ ማለት የመካከለኛ ሰው መዳፍ የሚሞላ ነው። ግዴታ ያደረጉትም ሁሉም ነፃ፣ ባሪያ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ህፃን፣ ትልቅ ሙስሊም ላይ ከተምር ወይም ከገብስ እንዲሰጡ ነው። ይህም እርሱ ዘንድ ያለው ከቀንና ከምሽት ቀለቡ የሚተርፍ በሆነ ላይ ለነፍሱና ለሚያስተዳድራቸው ሁሉ ነው። ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality