Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡

Available in 70 languages
«ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ "ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተኸዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከለከለውን ሀሜት ምንነት : ሙስሊምን በሌለበት በሚጠላው ነገር ማውሳት መሆኑን በመግለፅ አብራሩ። ይህም ተፈጥሯዊውም ሆነ ስነ ምግባሪያዊ ባህሪውን ቢያወሳ ተመሳሳይ ነው። እውሩ ፣ አጭበርባሪ ፣ ውሸታምና የመሳሰሉትን እሱ ላይ የሚገኙ የተወገዙ መገለጫዎችን በማውሳት ማማት ማለት ነው። የተወሱት እሱ ላይ የሌሉ ባህሪያት ከሆኑ ግን ከሀሜትም የባሰ ነው። እሱም መቅጠፍ (ቡህታን) ነው የሚሆነው :- ማለትም በሰው ላይ የሌሉበትን ባህሪያት መቅጠፍ ነው።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality