ሲራና ታሪክ
ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
Available in 48 languages
«ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስቶች ስለርሳቸው ድብቅ (ቤት ውስጥ የሚሰሩት) ዒባዳ ጠየቁ። (የርሳቸውን የቤት ውስጥ ስራ ከሰሙ በኋላ) አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ሴት አላገባም!" አንዱ ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም!" አለ። እርሳቸውም አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።»»Meaning translation ·
Saved at original quality








