Hadith for the World
የነቢዩ ሙሐመድ ስነ-ተፈጥሮ

ነቢያዊ መመሪያ

7 hadiths

7 hadiths

ከአማኞች እናት ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ ብላለች፦ «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሊት የተነሱ ጊዜ አፋቸውን በመፋቂያ ይፍቁ ነበር።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ከዘይነብ ቢንት ጀሕሽ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እርሷ ዘንድ እንዲህ አያሉ ደንግጠው ገቡ: "ላኢላሀ ኢለሏህ በቀረበው አደጋ ለዐረቦች ወዮላቸው! ዛሬ የየእጁጅና መእጁጅ ግድብ የዚህን ያህል ተከፍቷል።" አሉና በአውራ ጣታቸውና በጠቋሚ ጣታቸው ክብ አደረጉ። ዘይነብ ቢንት ጀሕሽም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በመካከላችን ደጋጎች እያሉ እንጠፋለን?" አለች። እርሳቸውም "አዎን ፀያፍ የበዛ ጊዜ" አሏት።ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عن عائشة رضي الله عنها قالت: كان رسولُ اللهِ صلى الله عليه وسلم إذا فَاتَتْهُ الصَّلَاةُ مِنَ الليلِ مِن وَجَعٍ أَوْ غَيْرِهِ، صَلَّى من النَّهَارِ ثِنْتَيْ عَشْرَةَ رَكْعَةً.رواه مسلم
ከአነስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የተወሰኑ የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሶሐቦች የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስቶች ስለርሳቸው ድብቅ (ቤት ውስጥ የሚሰሩት) ዒባዳ ጠየቁ። (የርሳቸውን የቤት ውስጥ ስራ ከሰሙ በኋላ) አንዱ እንዲህ አለ "እኔ ሴት አላገባም!" አንዱ ደግሞ "እኔ ስጋ አልበላም!" አለ። ሌላኛው ደግሞ "እኔ ፍራሽ ላይ አልተኛም!" አለ። እርሳቸውም አላህን ካመሰገኑና ካወደሱ በኋላ እንዲህ አሉ "እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።»ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: إِنَّ خَيَّاطًا دَعَا رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِطَعَامٍ صَنَعَهُ، قَالَ أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ: فَذَهَبْتُ مَعَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِلَى ذَلِكَ الطَّعَامِ، فَقَرَّبَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خُبْزًا وَمَرَقًا، فِيهِ دُبَّاءٌ وَقَدِيدٌ، فَرَأَيْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَتَتَبَّعُ الدُّبَّاءَ مِنْ حَوَالَيِ القَصْعَةِ، قَالَ: فَلَمْ أَزَلْ أُحِبُّ الدُّبَّاءَ مِنْ يَوْمِئِذٍ.متفق عليه
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قِيلَ: يَا رَسُولَ اللهِ ادْعُ عَلَى المُشْرِكِينَ قَالَ: «إِنِّي لَمْ أُبْعَثْ لَعَّانًا، وَإِنَّمَا بُعِثْتُ رَحْمَةً».رواه مسلم