Hadith for the World
Tap the image to view it full size
የተከበረው ቁርአንና ከቁርአን ጋር የተያያዙ እውቀቶች

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:

Available in 65 languages
«ከዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: 'ከአላህ መጽሐፍ አንዲትን ፊደል የቀራ ሰው ለርሱ አንዲት ምንዳ ይሰጠዋል። አንዲት ምንዳ ደግሞ በአስር አምሳያዋ (ትባዛለች።) (ይሄንን ስል) {አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማንኛውም ከአላህ መጽሐፍ አንድ ፊደል የሚቀራ ሙስሊም ለርሱ ምንዳ እንዳለውና አንዱ ምንዳ ደግሞ ለርሱ በአምሳያው እስከ አስር ድረስ እንደሚባዛለት ተናገሩ። ከዚያም ይህንን ({አሊፍ ላም ሚም} አንድ ፊደል ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን {አሊፍ} አንድ ፊደል ነው። {ላም} አንድ ፊደል ነው። {ሚም} አንድ ፊደል ነው።) በሚለው ንግግራቸው ሶስት ፊደል እንደሚሆኑና ሰላሳ ምንዳ እንደሚሆኑ ገለፁ።

Source
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality