Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:

Available in 42 languages
«ከአነስ ቢን ማሊክ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።"»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላት ውስጥ ሆነው ዱዓ ሲያደርጉም ይሁን ሌላ ድርጊት ሲያደርጉ አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎችን አስጠነቀቁ። ቀጥለውም ይህንን በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ ማስጠንቀቂያቸውንና ዛቻቸውን አበረቱ። በማያውቁት መልኩ የማየትን ፀጋ በሚያጡበት ሁኔታ አይኖቻቸውን የመነጠቅና በፍጥነት የመጥፋት አደጋ እንደሚፈራለትም አሳሰቡ።

Source
ቡኻሪ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality