Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም እርሱን ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖሮ ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:

Available in 60 languages
«ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም እርሱን ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖሮ ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐርን ልብስ በየትኛውም አይነቱ ከመልበስ ወንዶችን ከለከሉ። ወንዶችንም ሴቶችንም በወርቅና ብር እቃዎችና መሳሪያ ከመብላትና ከመጠጣት ከለከሉ። ይህም አማኞች በዚህች አለም አላህን ለመታዘዝ እንደራቁት ሁሉ የትንሳኤ ቀን ደግሞ ለአማኞች ብቻ እንደሆነ ተናገሩ። ከሀዲያኖችስ በመጪው ዓለም ምንም የላቸውም። ምክንያቱም የአላህን ትእዛዝ በማመፅ ቸኩለው በዚህ ዓለም ህይወታቸው ምርጥ የሚሉትን ነገሮች በመያዝ ስለተጠቀሙ ነው።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality