Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ትርፍ ተግባራትና ስነ-ስርዓት

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል:

Available in 62 languages
«ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: ‹ባሏ ለሞተባትና ለሚስኪን የሚለፋ ሰው ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ሰው አምሳያ ወይም ልክ ሌሊት እየሰገደ ቀኑን እንደሚፆም አምሳያ ነው›"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ባሏ ለሞተባትና የሚያስፈልጋትን ጉዳይ የሚያሟላላት አንድም ሰው ለሌላት ሴት እና ተረጂ ለሆነ ሚስኪን ጥቅማቸውን በሟሟላት የቆመ እንዲሁም አላህ ዘንድ ምንዳን በማሰብ ለነርሱ ወጪ የሚያደርግ ሰው በምንዳ ደረጃ ልክ በአላህ መንገድ እንደሚታገል ወይም ለተሀጁድ ሶላት ሳይደክም እየቆመ ምንም ቀን ሳያፈጥር እንደሚፆም ሰው አምሳያ መሆኑን ነቢዩ (የአሏህ ሶለዋትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) ተናገሩ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality