Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ሲራና ታሪክ

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል:

Available in 56 languages
«ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል: «ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከክፍሏ ከማትወጣ ልጃገረድ የበለጠ አይነአፋር ነበሩ። አንዳች የሚጠሉትን ነገር የተመለከቱ ጊዜ ፊታቸው ላይ ነበር የምናውቀው።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

አቡሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሳታገባና ወንዶች ጋር ሳትኗኗር በቤቷ ተሸሽጋ ከምትኖር ልጃገረድ ሴት የበለጠ አይነአፋር እንደነበሩ ተናገረ። እጅግ አይነአፋር ከመሆናቸው የተነሳ አንድ ነገር የጠሉ ጊዜ ፊታቸው ይለዋወጣል እንጂ አይናገሩም። ይልቁኑም ባልደረቦቻቸው ፊታቸውን በመመልከት ያንን ነገር መጥላታቸውን ይረዳሉ።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality