Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ሲራና ታሪክ

ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:

Available in 39 languages
«ከአቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «እኛ ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን የአጋርያን እግር ከጭንቅላታችን በላይ ሆኖ ተመለከትኩት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ: ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመለከተን ነበር።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉ።»»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

የአማኞች መሪ አቡ በክር አስሲዲቅ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በስደት ወቅት ስለነበረው ሁኔታ ሲተርኩ እንዲህ አሉ: እኛ የሠውር ዋሻ ውስጥ ሆነን ሳለን ከጭንቅላታችን በላይ የአጋርያን እግር ሆኖ ተመለከትኩ። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ከአጋርያኖች መካከል አንዱ ወደ እግሮቹ ቢመለከት'ኮ ከእግሮቹ ስር ይመከተናል።" አልኳቸው። እርሳቸውም: "አቡ በክር ሆይ! አላህ በእርዳታው፣ በእገዛውና በጥበቃው ሶስተኛቸው በሆኑ ሁለት ሰዎች ጉዳይ ምንድን ነው የምታስበው?" አሉት።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality