Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ፊቅህና የፊቂህ መርሆዎች

ከኡሙ ዐጢየህ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች:

Available in 40 languages
«ከኡሙ ዐጢየህ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "ጀናዛን ከመሸኘት ተከልክለናል። አፅንዖት ሰጥተው ግን አልከለከሉንም።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ኡሙ ዐጢየህ አልአንሷሪየህ (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሴቶች ጀናዛን ለመሸኘት አብረው ከመሄድ እንደተከለከሉ ተናገረች። ይህም ለነርሱም ይሁን በነርሱ ምክንያት ፈተና ይከሰታል ተብሎ ስለተፈራና ትእግስታቸው ያነሰ ስለሆነ ነው። ቀጥላም (አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና) ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሌሎች ክልከላዎች ላይ እንደሚያከብዱት ይህንን ግን ክብደት ሰጥተው አልከለከሉም አለች።

Source
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality