Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው

Available in 70 languages
«ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ካለውና ከጠራው አላህ ባወሩት (ሐዲሠል ቁድሲይ) አላህ እንዲህ ብሏል: "ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በነፍሴ ላይ እርም አድርጌያለሁ! በመካከላችሁም እርም አድርጌዋለሁ! ስለሆነም አትበዳደሉ! ባሮቼ ሆይ! ከመራሁት በስተቀር ሁላችሁም ጠማማ ናችሁና ምራቻን ከኔ ጠይቁ እመራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! ካበላሁት በስተቀር ሁላችሁም ረሀብተኞች ናችሁና መብልን ከኔ ጠይቁ እመግባችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እኔ ካለበስኩት በስተቀር ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁና ልብስን ከኔ ጠይቁ አለብሳችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ በሌሊትም ሆነ በቀን ትሳሳታላችሁ። እኔ ደግሞ ሁሉንም ወንጀሎችን እምራለሁ። ስለሆነም ምህረትን ከኔ ፈልጉ እምራችኋለሁ! ባሮቼ ሆይ! እናንተ እኔን ጉዳትን ልትጎዱኝ አትችሉም። ጥቅምን ልትጠቅሙኝ ዘንድም አትችሉም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም ከናንተ መካከል እንደሚገኝ አንድ እጅግ አላህን ፈሪ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይጨምርም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም ሁሉም እንደ አንድ እጅግ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰው ቢሆኑ ይህ ከንግስናዬ አንዳችም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ከመጀመሪያዎቻችሁ እስከመጨረሻዎቻችሁ ሰዎችም ጂኖችም በአንድ ሰፊ ሜዳ ላይ ቢቆሙና ቢጠይቁኝ ለእያንዳንዱም የጠየቀኝን ብሰጠው መርፌ ባህር የገባች ጊዜ እንደምትቀንሰው ያህል ካልሆነ በቀር ይህ (መስጠቴ) እኔ ዘንድ ካለው (ሀብት) ምንም አይቀንስም። ባሮቼ ሆይ! ይህቺ ስራችሁ ናት ለናንተ አስቀምጥላችኋለሁ ከዚያም እራሷን እመነዳችኋለሁ። ምንዳውን መልካም ሆኖ ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከዛ ውጪ ሆኖ ያገኘ ግን ከነፍሱ በስተቀር ማንንም እንዳይወቅስ።"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በደልን በነፍሱ ላይ እርም እንዳደረገና አንዱ አንዱን እንዳይበድል በደልን በፍጡራኑ መካከልም እርም እንዳደረገው መናገሩን አብራሩ። ሁሉም ፍጡራን በአላህ መምራትና መግጠም ካልሆነ በቀር ከእውነተኛው መንገድ የጠመሙ ናቸው። መመራትን ከአላህ የጠየቀ ሰው አላህም ይገጥመዋል ይመራዋልም። ፍጡራን በሁሉም ጉዳዮቻቸው ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸው። አላህን የጠየቀን ሰው አላህም ጉዳዩን ይፈፅምለታል ይበቃዋልም። ፍጡራን ሌት ተቀን ወንጀል ይፈፅማሉ። አላህ ደግሞ ባሪያው ምህረትን በሚጠይቀው ወቅት ይሸሽገዋልም ያልፈዋልም። ፍጡራን አላህን አንዳችም ሊጎዱም ወይም ሊጠቅሙ አይችሉም። ፍጡራን ሁሉ እንደ አንድ አላህን እጅግ የሚፈራ ቀልብ ያለው ግለሰብ ቢሆኑ ፍራቻቸው በአላህ ንግስና ላይ አትጨምርም። ሁሉም እንደ አንድ ጠማማ ቀልብ ያለው ሰውዬ ቢሆኑም ጥመታቸው በንግስናው ላይ አንዳችም አይቀንስም። ምክንያቱም ደካሞችና ወደ አላህ ፈላጊዎች ናቸውና። በሁሉም ሁኔታ፣ ዘመንና ስፍራ ወደርሱ ፈላጊዎች ናቸው። የተብቃቃም እሱ ብቻ ነው። ፍጡራን ሁሉ ሰዉም ጋኔኑም ከመጀመሪያቸው እስከመጨረሻቸው አላህን ለመጠየቅ በአንድ ስፍራ ላይ ቢቆሙና ከነርሱም ለእያንዳንዱ ሁሉ የጠየቀውን ቢሰጥ ይህ መስጠቱ አላህ ዘንድ ካለው አንዳችም አይቀንስም። ልክ እንደ መርፌ ባህር ውስጥ ገብታ ብትወጣ ባህሩ በዚህ አንዳችም እንደማይቀነሰው ማለት ነው። ይህም የሆነው ከተሟላው ሀብቱ አንፃር ነው። ጥራት ተገባው! ጥራት የተገባው አላህ የባሮችን ስራዎች ይጠብቃልም ያስቀምጣልም። ከዚያም እሷኑ የትንሳኤ ቀን ይመነዳቸዋል። የስራውን ምንዳ መልካም ሆኖ ያገኘው ሰው አላህ ትእዛዙን ለመፈፀም ስለገጠመው አላህን ያመስግን። የስራውን ምንዳ ከዚህ ውጪ ሆኖ ያገኘ ሰውም ወደ ክስረት የመራችውን በመጥፎ የምታዘው ነፍሱን እንጂ ሌላን እንዳይወቅስ።

Source
ሙስሊም ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality