Hadith for the World
Tap the image to view it full size
ዐቂዳ (እምነት)

ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

Available in 61 languages
«ከአቡ በርዛህ አልአስለሚይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል: "የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'"»

Meaning translation ·

Explanation

The meaning in a few plain lines

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከሒሳብ መተሳሰቢያ ስፍራ አንድም ሰው ስለተወሰኑ ጉዳዮች ሳይጠየቅ ወደ ጀነት ወይም ወደ እሳት እንደማያልፍ ተናገሩ። የመጀመሪያው: ህይወቱን በምን እንዳጠፋውና እንዳሳለፈው? ሁለተኛው: ዕውቀቱን ለአላህ ብሎ ነው የፈለገው? በእውቀቱ ሰርቶበታልን? ማወቅ ለሚገባውስ አስተላልፎታልን? ሶስተኛው: ገንዘቡን ከየት ነው ያገኘው? ከሐላል ነው ወይስ ከሐራም? ለምንስ አዋለው? አላህን በሚያስደስት ነገር ላይ አዋለው? ወይስ በሚያስቆጣው ነገር ላይ? አራተኛው: ስለ አካሉ፣ ሀይሉ፣ ጤንነቱ፣ ወጣትነቱ ነው። ምን ላይ ተጠቅሞ እንዳሳለፈው?

Source
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
Download image

Saved at original quality